በአሏህ ስም እጅግ በጣም ርህሩህ እጅግ በጣም አዛኝ በሆነው።
=<({አል-ኢኽላስ 112:1-4})>=
ﺑﺴﻢ ﺍﻟﻠﻪ ﺍﻟﺮﺣﻤﻦ ﺍﻟﺮﺣﻴﻢ
1. በል! እርሱ አላህ አንድ ነው።
2. አላህ (የሁሉ) መጠጊያ ነው።
3. አልወለደም፤ አልተወለደምም።
4. ለእርሱም አንድም ብጤ የለውም።

 =<({አል-ቁርአን 96:1-5})>=
ያ ሁሉን በፈጠረው ጌታህ ስም አንብብ!
በቡኻሪ በተዘገበው ሐዲስ መሰረት እውቀትን መሻት በእያንዳንዱ ሙስሊም ላይ ግዴታ ነው።  |
۩۞۩ እራሳችነን ሳንለውጥ ሌሎችን መለወጥ ለምን አስፈለገን?۩۞۩
ዛሬ የብዙወቻችን ችግር ኢልም አይደለም ተግባሩ እንጂ። ብዙወቻችን አንብበናል ፣ ሰምተናል ፣ አውቀናልም ነገርግን ከአስተማሪውም ሆነ ከተማሪው የተግባር ሰው ጠፍቷል። መካሪው እና ተመካሪው እኩል ሆኗል!!!
በእርግጠኝነትና በቆራጥ ውሳኔ መንቃት የምንፈልግ ሁሉ በዚህ የቁርአን አንቀፅ እንንቃ!!!
አሏህ በቁርአኑ በሱረቱ አል-ሶፍ አንቀፅ 2 ላይ እንዲህ ይላል:-
=<({አል-ቁርአን 61:2})>=
{2} እናንተ ያመናችሁ ሆይ የማትሰሩትን ነገር ለምን ትናገራላችሁ።
በሱረቱል በቀራ አንቀፅ 44 ላይ እንዲህ ይላል:-
=<({አል-ቁርአን 2:44})>=
{44} እናንተ መጽሐፉን የምታነቡ ሆናችሁ ሰዎችን በበጎ ስራ ታዛላችሁን? ነፍሶቻችሁንም ትረሳላችሁን? የስራዎቻችሁን መጥፎነት አታውቁምን?
አይሁዶች መጽሐፍ ተሰቷቸው ስላልተስራሩበት በአህያ ተመሰሉ አሏህ በቁርአኑ በሱረቱል ጁምአ አንቀው 5 ላይ እንዲህ ይለላል:-
=<({አል-ቁርአን 62:5})>=
{5} የእነዚያ ተውራትን የተጫኑትና ከዚያም ያልተሸከሟት(ያልሰሩባት) ሰዎች ምሳሌ መጽሐፎችን እንደሚሸከም አህያ ቢጤ ነው። የእነዚያ በአሏህ አንቀጾች ያስተባበሉት ህዝቦች ምሳሌ ከፋ። አሏህም በዳዮችን ህዝቦች አይመራም።
©የወጣቱ ተልእኮ
۩۞۩ Youth-Mission
የወጣቱ ተልእኮ-> page۩۞۩
page:
http://facebook.com/youth.mission29
website:
http://youth-mission.mobie.in
'~'-.,__,.-'~'
_,.-'~''~'-.,_
735